በሆስፕታሊቲ ዘርፉ ላይ የሚታየውን የሰለጠነ ሰው ሀይል እጥረት ለመቅረፍ ውይይት ተካሄደ
Apr 09, 2025
በቱሪዝም ሴክተሩ ካሉ አደረጃጀቶች ጋር በሰለጠነ የሰው ሃይል ልማትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡
በዘርፉ ያለውን የሰለጠነ የሰው ሃይል አቅርቦትን ለማሻሸል፣ የመንግስትና የግሉን ዘርፍ ትብብርና ቅንጅት ለማጠናከር እና እሴት ሰንሰለቱን መሰረት በማድረግ ጥራት ያለው የሥራ ዕድል መፍጠር የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ምክክር ተደርጓል፡፡
በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር ፕሬዝዳንትን ጨምሮ የኢትዮጵያ ሆቴልና ቱሪዝም አሰሪዎች ፌደሬሽን፣ የኢትዮጵያ ቱር ኦፐሬተርስ ማህበር እና ታላቅ ኢትዮጵያ አስጎብኝዎች ማህበር ፕሬዝዳንቶች የተገኝተዋል፡፡
1250 Eye Street, N.W., Suite 1100
Washington, D.C. 20005
Ethiopian Tourism Transformation Council
Ethiopian Industry Transformation Member
Entoto poly Technic College Technical Advisory Board