news-header-image

በከፍተኛ ትምህርት፣ ስልጠና፣ የምርምር ተቋማት እና የኢንዱስትሪ ትስስር ፎረም ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

የከፍተኛ ትምህርት፣ ስልጠና፣ የምርምር ተቋማት እና የኢንዱስትሪ ትስስር ፎረም

Jul 01, 2025

2 minute read

የከፍተኛ ትምህርት፣ ስልጠና፣ የምርምር ተቋማት እና የኢንዱስትሪ ትስስር ፎረም የሀገራችንን ኢንዱስትሪዎችና ትምህርት ተቋማትን ለማስተሳሰር በአዋጅ ቁጥር 1298/2015 በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቋቋመ ነው፡፡


ፎረሙ ትኩረት ከሚያደርግባቸው መካከል የሆቴል እንዱስትሪውን የሚያካት የቱሪዝምና ትራንስፖርት እንዱስትሪ ትስስር ፎረም ሲሆን የኢንዱስትሪ ትስስር ፎረሙ የተግባር ልምምድና እና የትብብር ስልጠና፣ የጋራ ችግር ፈቺ ምርምር፣ የማማከር አገልግሎት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር መሆኑን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናውን የሰጡት አቶ ተሾመ ዳንኤል ገልጸዋል፡፡

ይህ ፎረም የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ወደ ትምህርት ተቋም ሂደው የሚያሰልጥኑበት፣ የትምህርት ተቋማት ያሉ መምህራንም ወደ ኢንዱስትሪው ወጥተው በተግባር እውቀታቸውን የሚያሳድጉበት እድል የሚፈጥር መሆኑን የገለጹት አቶ ተሾመ ዳንኤል በሌላ በኩል በኢንዱስተሪና ስልጠና ተቋማት ላይ የሚታዩ ችግሮችን በጋራ ጥናት የሚደረግበት እንዲሁም ከአንዱስትሪ ወደ ትምህርት ተቋማት/ከትምህርት ተቋማት ወደ ኢንዱስትሪ / የቴክኖሎጂ ሽግግር የሚደረግበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ይህ የኢንዱስትሪ ትስስር ፎረም የራሱን ፈንድ እንዲኖረው እየተሰራ የሚገኝ መሆኑን የተናገሩት አቶ ተሾመ ኢንዱስትሪው እና የትምህርትና ስልጠና ተቋማት በመመሪያ የተደገፈ በጋራ ወጪ በማዋጣት ለሚሰሩ ችግር ፈቺ ምርምሮችና ቴክኖሎጂዎች ውጤታማ እንዲሆን ይሰራል ብለዋል፡፡


ይህ የኢንዱስትሪ ትስስር ፎረም የሰለጠነ የሰው ሀይል ችግርን ለመፍታት፣ ችግር ፈቺ ምርምሮችን ለማድረግ፣ ሀገር በቀል ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች እንዲኖረን የሚያግዝ ሲሆን ሁሉም እንዱስትሪ የበኩሉን መወጣት የሚገባ ሲሆን በኢንዱስትሪ ትስስር ፎረም አዋጅና እየተዘጋጀ በሚገኘው መመሪያ መሰረት ለግል ዘርፉ ማበረታቻና ድጋፍ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡


የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር በዚህ የኢንዱስትሪ ትስስር ፎረም ውስጥ አባል በመሆን በተለይ የሆቴል ዘርፉን ዘላቂ እድገት የሚደግፉ ሀሳቦችን በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡

logo

Your Source for Addis's Hotel Updates

logo

1250 Eye Street, N.W., Suite 1100

Washington, D.C. 20005

We are Members Of

Ethiopian Tourism Transformation Council

Ethiopian Industry Transformation Member

Entoto poly Technic College Technical Advisory Board

AHA 2025. All rights reserved