ቀጠናዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው
May 06, 2025
ኢትዮጵያን ጨምሮ ከምስራቅ አፍሪካ፣ ከአውሮፖ እና ከኤዥያ ልዩ ልዩ ሀገራት የሚሳተፉበት በጂኦፖርኮች እና ጂኦቱሪዝም ላይ የሚመክር ቀጠናዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው፡፡
#AHA ሚያዝያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም
የቱሪዝም ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት /UNESCO/ ጋር በመተባበር ከግንቦት 4-7 /2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚያካሄደውን የመጀመሪያውን የጅኦ-ፓርኮች እና የጅኦ ቱሪዝም ለዘላቂ ልማት ያላቸውን ፋይዳ ለማጉላትና ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ቀጠናዊ መድረክ መዘጋጀቱን ቱሪዝም ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
መድረኩ በጅኦፓርክ እና በጅኦ ቱሪዝም ላይ የባለድርሻ አካላትን ግንዛቤ በማሳደግና አቅማቸውን በማጠናከር በኢትዮጵያ እንዲሁም በሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የGlobal Geoparks ፕሮጀክቶችን ለማስጀመር የሚያስችል መነቃቀት መፍጠር እንደሆነ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ገልጸዋል፡፡
በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (UNESCO) ካንትሪ ዳይሬክተር ዶክተር ሪታ ቢሶናውት በበኩላቸው ዩኔስኮ እስካሁን በ50 ሀገራት 229 ዓለም አቀፍ ጂኦፖርኮችን ለይቶ ጥበቃ እያደረገ እንደሆነ ገልፀው በአፍሪካ በተለይ በምስራቅ አፍሪካ ብዙ የጂኦፖርኮ ሀብቶች ያሉ በመሆኑ ሀገራቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መዳረሻዎችን በማልማት ተጨማሪ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎችን ለማስፋት እየሠራ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
1250 Eye Street, N.W., Suite 1100
Washington, D.C. 20005
Ethiopian Tourism Transformation Council
Ethiopian Industry Transformation Member
Entoto poly Technic College Technical Advisory Board