news-header-image

የሆቴሎች ደረጃ ምደባ ይፋ ተደረገ

በመዲናዋ የሚገኙ አርባ ሆቴሎች ደረጃ ምደባ ይፋ ተደረገ

May 29, 2025

2 minute read

በመዲናዋ የሚገኙ 11 ሆቴሎች የባለ አምስት ኮከብ ደረጃ አገኙ።


AHA ግንቦት 21፣ 2017 ዓ.ም


የቱሪዝም ሚኒስቴር በ2017 ዓ.ም በ92 ሆቴሎች ላይ ሲያደርግ የቆየውን የደረጃ ምደባ ይፋ አድርጓል።

ሚኒስቴርሩ ባደረገው የደረጃ ምደባ ስድስት አዲስ ሆቴሎችን ጨምሮ 40 ሆቴሎች በኮከብ ደረጃ ውስጥ ገብተዋል።

ቀደም ሲል በኮከብ ደረጃ ውስጥ የነበሩ 15 ሆቴሎች ደግሞ በተለያዩ ምክንያቶች ኮከባቸው ተወስዷል።


የኮከብ ደረጃ ከተሰጣቸው ሆቴሎች መካከል 11 ሆቴሎች የባለ 5 ኮኮብ ደረጃ አግኝተዋል። በተመሳሳይ 11 ሆቴሎች ባለ 4 ኮከብ ደረጃ ሲያገኙ፤ ዘጠኝ ሆቴሎች ባለ ሶስት፣ ሰባት ሆቴሎች ባለ ሁለት እንዲሁም 2 ሆቴሎች ባለ አንድ ኮኮብ ደረጃ ተሰጥቷቸዋል።

አሁን የተሰጠው ደረጃ ለሶስት ዓመት የሚያገለግል እንደሆነም ተገልጿል።


የተደረገው የሆቴሎች የደረጃ ምደባ የቱሪዝም ዘርፉን የሚደግፍና ቱሪስቶችን የሚስብ እንደሆነ ሲነሳ አሁን በአዲስ አበባ እየተስፋፋ የመጣውን የኮንፈረንስ ቱሪዝምን ያግዛል።

logo

Your Source for Addis's Hotel Updates

logo

1250 Eye Street, N.W., Suite 1100

Washington, D.C. 20005

We are Members Of

Ethiopian Tourism Transformation Council

Ethiopian Industry Transformation Member

Entoto poly Technic College Technical Advisory Board

AHA 2025. All rights reserved