የአምስት ዓመት ዕቅድ ውይይትና ትውውቅ
May 10, 2025
የማህበሩ የቦርድ አባላት ትውውቅና በቀጣይ አምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ውይይት ተደረገ፡፡
ግንቦት 02/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር ቦርድ አባላት የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ትውውቅና
በማህበሩ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ውይይት ተደረገ፡፡
ማህበሩ ከ2024-2028 (እ.አ.አ) ድረስ የአባላቱን ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግና ማህበሩን ለማጠናከር በያዛቸው የስትራቴጂክ ዕቀድ ላይ ውይይትና የካቲት 22/2017 የቦርድ ምርጫ ተከትሎ የስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት ትውውቅ ተከናውኗል፡፡
የማህበሩ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ አስቴር ሰለሞን ማህበሩ የተቋቋመለትን ዓላማ ለማሳካት ከተለያዩ መስሪያቤቶች ጋር ጤናማ ግንኙነት በመፍጠር እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው፣ በዚህ ውስጥ ትብብር ላደረጉ አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ወ/ሮ አስቴር ባለፉት ሰባት ዓመታት በቦርድ አባልነት እንዲሁም በምክትል ፕሬዝዳንትነት ማህበሩን ሲመሩ ለበነበሩ አቶ መላኩ ሲማ ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሳው ማህበሩ ለሆቴል ዘርፉ እድገት ግብዓት የሚሆኑ ሃሳቦችን ሲያቀርብ የነበረ፣ የአባላቱን ችግሮች ለመፍታት ጠንክሮ እየሰራ የሚገኝና የተሻለ እንቅስቃሴ እያደረገ ያለ ማህበር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በዚህ ዘርፍ ያሉ ማህበራት ሲጠናከሩ የሀገራችን ቱሪዝም ያድጋል፣ ፖሊሲዎችን ለመተግበር ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር የገለጹት ዶ/ር ሂሩት ካሳው ማህበሩ አሁንም በሆቴል እንዱስትሪ ውስጥ የተሸሉ ልምዶችን በማምጣት ለሆስፕታሊቲ ዘርፉ የሃሳብ ምንጭ ሆኖ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡ ማህበሩ ተጠናክሮ እንቀጥል ቢሯቸው የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡
ማህበሩን በፋይናንስ ከማጠናከር፣ ማህበሩ ለአባላቱ የሚሰጠውን አገልግሎት ከማጠናከር፣ የመተግበር አቅምን ከማሻሻልና የጫና የመፍጠር አቅሙን እንዲያሳድግ በስትራቴጂው ውስጥ ተካተው ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
1250 Eye Street, N.W., Suite 1100
Washington, D.C. 20005
Ethiopian Tourism Transformation Council
Ethiopian Industry Transformation Member
Entoto poly Technic College Technical Advisory Board